የአፍሪካ 10ኛው የፐብሊክ ሰርቪስ ቀን

የአፍሪካ 10ኛው የፐብሊክ ሰርቪስ ቀን ከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር እና የተመድ የአፍሪካ ቀጣናዊ ፎረም በተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄድ ቆይቶ ተጠናቀዋል። +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ መድረኮቹ ስኬታማ መሆናቸውን እና የኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርም ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 እና ከመንግስታቱ ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ገልፀው፤ በዓለም ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋምና ቀድሞ ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትን መፍጠር ይገባል ብለዋል። በመሆኑም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለውን ውስብስብ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ አዳዲስ ፈጠራዎችና ሞዴሎችን ገቢራዊ ማድረግ ኃላፊው ያሉ ሲሆን፤ የመንግሥት አገልግሎት በአፍሪካ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ፤ በአገልግሎት ሰጭዎች ላይ የክህሎት፣ የአመራርና የትብብር አቅምን ማጎልበት ለአህጉራዊ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን በሪፎርም ላይ መሆኗን አንስተው፥ ለዜጎች ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሶብ የተሰኘ መሰረታዊ ተቋም መገንባቷን ገልጸዋል፡፡ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፅንሰ ሀሳብ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት የመነጨ መሆኑን ጠቅሰው፤ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሁሉም ዜጎች የቦታ ርቀት ወይም ሁኔታዎች ሳይገድቧቸው ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር መሆኑን አቶ አደም አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት ሪፎርም አካታች መሆኑን ጠቁመው፤ ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 እና ከተመድ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር ተቋማዊ ተጠያቂነትን ማስፈንና የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ልምዶች የተገኙበት መሆኑን ተናግረዋል። ዲጂታላይዜሽን፣ አቅም ግንባታ እና ፈጠራ የታከለበት አሰራሮች ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር)፥ አህጉራዊ ጉባኤው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ለዜጎች ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ጠንካራ ውሳኔ ተላልፎበታል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎትን በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጓዘችበትን ርቀት ታሳቢ በማድረግ ቀጣዩን ጉባኤ በድጋሚ እንድታስተናግድ መመረጧን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም እንግዶች በስካይ ላይት ሆቴል የእራት ግብዣ የተጋበዙ ሲሆን በተለያዩ (Most Accountable and Transparent Organization Award ,Best Managed Organization Award, Best Pavilion Award, Best Innovation in Service Delivery Award) በአራት ዘርፎች አሸናፊ ለሆኑት ሀገራት ከዕለቱ የከክብር እንግዳ ከሆኑት ክብርት ወ/ሮ አለም ፀሀይ ጳውሎስ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡

Share this Post